×
ፈልግ
ስለህይወት እና ስለእግዚአብሄር በነፃነት
 ጥያቄ የሚጠይቁበት ድረገጽ
ወሲብ እና የፍቅር ግንኙነት

የሴቶች መብት

WhatsApp Share Facebook Share Twitter Share Share by Email More PDF

በማርሊን አዳምሰን

ብዙ ጊዜ ኃይማኖቶች ስለሴቶች ባላቸው አመለካከት በሴት መብት ተከራካሪዎች ይነቀፋሉ። መሆንም አለበት። በመላው ዓለም የሴቶችን ክብረ የሚነኩ አያሌ ምሣሌዎችን ማግኘት ተችላላቸሁ። እነዚህ የሴት መብት አስከባሪ ድርጅቶች የማያውቁት ነገር ቢኖር ጌታ ኢየሱሰ ክርስቶስ ዕውነተኛ የሴቶች መብት አክባሪና አጋራቸው እንደሆነ ነው።

ከ2000 ዓመታት በፊት በእሥራኤል ምድር እየሱስ በኖረበት ዘመን የኃይማኖት መሪዎች እግዚአብሔር ሆይ ሴት አድርገህ ስላልፈጠርከኝ አመሰግንሃለሁ ይሉ ነበር። እየሱስ ግን ስለሴቶቸ ያለው አመለካከት በጊዜው በመካከለኛ ምሥራቅ ውስጥ ካለው አመለካከት እጅግ ፍጹም የተለየ ነበር። በዚያ ሴቶች የሚታዩት እንደ ሰው ሳይሆን ከአንድ ቁስ ተለይተው አይታዩም ነበር። ስለዚህም በማህበራዊ ጉዳይ ውስጥ ሚናቸው በብዙ የተገደበና አስፈላጊነታቸው ለባሎቻቸውና ለልጆቻቸው ብቻ ነበር። አንድ የአይሁድ ዕምነት መምህር በቤተ መቅደስ ውስጥ ኃይማኖታዊ ሥርዐቱን ሲፈጽም ምንም ቅር ሳይለው የተባረክከው አምላካችን ሆይ ሴት አድርገህ ስላልፈጠርከኝ አመሰግንሃለሁ ብሎ ይጸልያል ። ሁሉም ሴቶች በማንኛውም በጉባኤ ከሚደረገው ኃይማኖታዊ ሥርዓት የተገለሉ ናቸው። የሙሴን ሕግ ቶራ የሚባለውን የአይሁድ ዕምነት ቅዱስ ዕምነት መጽሐፋቸውን በግላቸውመ ቢሆን እንኳ የተማሩት ጥቂት እጅግ በጣም ጥቂት ናቸው።

አንድ አይሁዳዊ ባል ሚስቱን ያለምንም ምክንያት ይፈታት ዘንድ ሕጉ ይፈቅድለት ነበር። ለምሳሌ እራት በጊዜ ካላዘጋጀች ለመፈታት በቂ ምክንያት ነበር፡፤ ሚስት ይህን እርምጃውን ለመቃወም የሚያስችላት ምንም መብት የላትም። በቀላሉ የፍችዋን ጽሕፈት አዘጋጅቶ መስጠትና ማባረር ብቻ ነው ከባልየው የሚጠበቀው። ይታያችሁ ይህ ሕግ ሴቶችን ምን ያህል አለኝታ እንዳሳጣቸውና ክፉኛ እንደጨከነባቸው፡፡ በአንጻሩ ሚስቶች ባሎቻቸውን በራሳቸው ፈቃድ መፍታት ፋጽሞ አይችሉም። በምንም ምክንያት።

በተወሰኑ ዐረብ አገሮች ውስጥ ውስጥ አሁንም እንኳ በሴቶቸ ላይ ተግባራዊ እገዳ የሚያደርግ ሃይማኖትና ባህል አለ። ሴት ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል ተሸፋፍና እንድትሄድ የሚያስገድድ ተግባራዊ የሚያደርጉ የዐረብ አገሮች ብዙ ናቸው። ሴት ብቻዋንም ሆነ ከጓደኛዋ ጋር ከቤት እንድትወጣ አይፈቀድላትም። ከወንድ ጋር እንጂ ብቻዋን በአደባባይ በሚከበር ክብረ በዐል ላይ እንድትገኝ ከቶም አይፈቀድላትም። በአንዳንድ የአረብ አገር ውስጥ ሴቶች መኪና እንዲነዱ አይፈቀድላቸውም። እንደዚሁም ባሎቻቸው ሊላ ሚስት ሲያገቡ ምንም የተቃውሞ ድምጽ እንዲያሰሙም አይፈቀድላቸውም።

ኢየሱስ ክርስቶስ በአደባባይ ከሚያስተምራቸው ደቀመዛሙርቶቹ መካከል በርካታ ሴቶች ነበሩ። ሕዝቦች ሲሰበሰቡና ሲያስተምርም ወንዶችም ሴቶችም አንድ ላይ ተደባልቀው ያስተምራቸው ነበር። ሴቶችን ከወንዶች ሳይለይ ተዓምራትን በሕይወታችው ፈጽሟል።

ፊሊፕ ያንሲ የተባለ አንድ ጸሐፊ ፡- « ለሴቶቸና ለተጨቆኑት ሰዎች ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የጊዜውን ሕግና ጥበብ እንዳልነበረ አድርጎ ገለባብጣታል። ጌታ ኢየሱስ በማህበረሰቡ ውስጥ ዋንኛና ተገቢ ነው ብለው የተቀበሉትን የአኗኗር ዘይቤ በተለይም የሴቶችን መብት በማክበርና በመጠበቅ እንዳሳየ በአራቱ ወንጌላት ውስጥ አንብቦ መረዳት ይቻላል ። » አለ።

እጅግ ብዙ የሆኑ ሰዎች ኢየሱስን ተከተሉት። ገሚሱ ተዓምራት እንዲያደርግላቸው፤ ገሚሱ እንዲያስተምራቸው፤ ይከተሉት ነበር፤ ዝናው በጅማሬው ላይ በራሱ ላይ ችግር ፈጥሮበት ነበር። የሃይማኖት ባለሥልጣናት ይህ ሁኔታ አልተመቻቸውም ፤ ስለዚህ እርሱን በነገር ሊያጠምዱት ዕቅድ አወጡ።

እነሱም ሆነ ሌሎችም ኢየሱስ ክርስቶስ ስለሚያስተምረው ስለፍቅር፣ ስለምህረትና ፣ስለርህራሄ ሰምተዋል። የሃይማኖት መሪዎቹ ይህንን ለማጥመጃ እንዲሆናቸው አድርገው ሊጠቀሙበት ፈለጉ።

ከሃይማኖት ሕጎቻቸው ውስጥ በተለይም ሴቶችን አስመልክቶ እጅግ ከባዱ የሚባለውና በድንጋይ ተወግረው እንዲገደሉ የሚደነግገው ሕግ አንዲት ሱት በዝሙት ምክንያት ከተያዘች ነበር። ስለዚህ ሕዝቡን አስተባበሩና አንዲትን ሴት በዝሙት ይዘው ለመገደል አመቻችተው እሱንም ለማጥመድ አድርገው በጌታ ኢየሱስ ፊት አቀረቧት። ምናልባትም ይቺ ሴት ከአንድ ጓደኛቸው ጋ ይሆናል የያዝዋት፤ ከዚያም ለጌታ ኢየሱስ እንዲህ አሉት፡-

መምህር ሆይ፥ ይህች ሴት ስታመነዝር ተገኝታ ተያዘች። ሙሴም እንደነዚህ ያሉት እንዲወገሩ በሕግ አዘዘን፤ አንተስ ስለ እርስዋ ምን ትላለህ? አሉት። ዮሐ 8፥3-4

አሁን ገና አገኘነው ብለው ነው ያሰቡት። መፈናፈኛ እንዳሳጡት አድርገው ነው የቆጠሩት። ምህረት ቢያደርግላት ዝሙትን እንደደገፈና የሙሴን ሕግ እንዳቃለለና የሙሴ ሕግ ጠላት እንደሆነ በቂ ማረጋገጫ አገኙ ማለት ነው። በአንጻሩ ሴቲቱን እንደ ሙሴ ሕግ ልክ እንዳሉት አንድትወገር ቢፈርድ፣ የሴቶችን መብት የማክበር ፋይዳው ምንም እንዳልሆነ ይታይና ስለምህረት ፣ ስለፍቅርና ስለቸርነት የሚያስተምረው ትምህርት እንደው ለማስተማር ብቻ እንጂ ሕይወት የለውም ማለት ነው ለማለት ተዘጋጅተዋል።

ታዲያ ምን ሆነ መሰላችሁ!

የሚከሱበትንም እንዲያገኙ ሊፈትኑት ይህን አሉ። ኢየሱስ ግን ጐንበስ ብሎ በጣቱ በምድር ላይ ጻፈ፤ መላልሰው በጠየቁት ጊዜ ግን ቀና ብሎ። ከእናንተ ኃጢአት የሌለበት አስቀድሞ በድንጋይ ይውገራት አላቸው። ደግሞም ጐንበስ ብሎ በጣቱ በምድር ላይ ጻፈ። ዮሐ 8፥6-7

ከዚህ በኋላ ማንም እዚያ ለመቂየት የደፈረ አልነበረም። ከታላቁ ጀምሮ ሁሉም አንድ በአንድ ሄደ። ኢየሱስና ሴቲቱ ብቻ ቀሩ።

እነርሱም ይህን ሲሰሙ ሕሊናቸው ወቀሳቸውና ከሽማግሌዎች ጀምረው እስከ ኋለኞች አንድ አንድ እያሉ ወጡ፤ ኢየሱስም ብቻውን ቀረ ሴቲቱም በመካከል ቆማ ነበረች።ኢየሱስም ቀና ብሎ ከሴቲቱ በቀር ማንንም ባላየ ጊዜ። አንቺ ሴት፥ እነዚያ ከሳሾችሽ ወዴት አሉ? የፈረደብሽ የለምን? አላት። እርስዋም፦ ጌታ ሆይ፥ አንድ ስንኳ አለች። ኢየሱስም፦ እኔም አልፈርድብሽም፤ ሂጂ ከአሁንም ጀምሮ ደግመሽ ኃጢአት አትሥሪ አላት። ዮሐ.8፥9-11

ምን ይደንቃል ጌታ ኢየሱስ አልፎ በተሰጠበትና በመስቀል ላይ ተሰቅሎ በሞተበት ጊዜ ወንዶቹ እግሬ አውጪኝ ብለው ሲሸሹ እስከ መስቀሉ ድረስ ከዛም አልፎ ነፍሱ እስክትወጣና እስከመቃብር ድረስ ሴቶች ተከትለው በመሄድ ፍቅራቸውን ቢገልጹልት ምን ይደንቃል?

ኢየሱስን ሞትን ድል አድርጎ በተነሳ ጊዜ የርሱን ከሞት መነሳት ያበስሩ ዘንድ ሴቶችን ለዚህ ታላቅ የምሥራች ተናጋሪ አድርጎ በመምረጥ አከበራቸው። ሴቶች ለቁም ነገር በማይታሰብቡበት በሕግና በሃይማኖት ጭቆና ቀንበር ስር ባሉበት ማህበረሰብ ውስጥ ሴትን የአንድ ታላቅ ዕምነት ድንቅ የትንሣኤውን መረጃ ለማቀበል አፈቀላጤ አድርጎ መለየት ይህ ታላቅ ነገር ነው።

ግን ለምን? የመጣው ለወንዶችም ለሴቶችም ኃጢዓት ሲል ለመሞት እንደሆነ በመጨረሻ አጠንክሮ በተጨባጭ ለማስቀመጥ ሊሆን ይችላል። ምናልባትም ሁለቱንም ወንዶችንም ሴቶችንም ሙሉ ይቅርታ እንዳደረገላቸውና ለሰላምና ለዘላለም ሕይወት እኩል ወራሽነት በዚህ መልክ ለማጽናት ፈልጎ ይሆናል።

በተጨማሪም ይህንን ዕውነት በተጨባጭ ከሳምራዊቱ ሴት ጋር ባደረገው ጭውውት በሚገባ አሳይቷል። በትችትና በነቀፋ ከማህበረሰቡ መገለልና መድልዎ የደረሰባትን ምሥኪን ሴት ውሃ በምትቀዳበት ቦታ ጠብቋት አነጋገራት። አምስት ጊዜ አግብታ ፈታለች። ይታያቸሁ አምስት ወንዶት ተፈራርቀው ተጠቅመውባት እንደ ዕቃ በንቀት ጥለዋት ሄደዋል። ይህ ምን ስሜት ውስጥ እንደሚከት ማሰቡ ይከብዳል። ጌታ ኢየሱስ ግን ሊያናግራት ውሃ ወደ ምትቀዳበት ጉድጓድ ድረስ መጣና እንዲህ አላት

« ። ኢየሱስም መልሶ፦ ከዚህ ውኃ የሚጠጣ ሁሉ እንደ ገና ይጠማል፤እኔ ከምሰጠው ውኃ የሚጠጣ ሁሉ ግን ለዘላለም አይጠማም፥ እኔ የምሰጠው ውኃ በእርሱ ውስጥ ለዘላለም ሕይወት የሚፈልቅ የውኃ ምንጭ ይሆናል እንጂ አላት። ዮሐ 4፥13-14

የጌታ ኢየሱስ ፍላጎት ሁልጊዜም እንደዚህ ነው። የርሱን ሕይወት ለዘላለም እንድንለማመድ ነው የሚፈልገው።

 ከእግዚአብሔር ጋር ግንኙነትን እንዴት እንደምትጀምር
 ጥያቄ አለኝ

ሼር ያድርጉ
WhatsApp Share Facebook Share Twitter Share Share by Email More