በሞህድ ሳሊም
እኔ ምንም እንደማያውቅ ዕድሜውን ካሳለፍኩ ተራ ሰው አልለይም ነበር። የተወለድኩት በፓኪስታን ውስጥ ሀብታም በሆነ ሙስሊም ቤተሰብ ውስጥ ቢሆንም ተወልጄ ጥቂት ወራት በነበርኩበት ጊዜ አባቴ ወደ ሳዑዲ አረቢያ ወሰደኝ። ስድስት ዓመት ሲሆነኝ እናቴ አረፈች። እያደግሁ ስሄድ እንደማንኛውም ሰው በሕይወት ውስጥ ብዙ ጥያቄዎች ነበሩኝ። ለምን እዚህ መጣሁ? ከየት መጣሁ? በእውነት እግዚአብሔር አለ እና ካለስ የት ነው? ለምን አይናገረኝም?
ከ12 ዓመቴ አካባቢ ጀምሮ ቁርአንን አጠና ነበር። በኋላም እንደነቢዩ ሙሐመድ ሕይወት፣ ሀዲሶችን፣ ወዘተ ያሉ ሌሎች የእስልምና መጻሕፍትን ማንበብ ጀመርኩ። እንደአብዛኛው የሳውዲ ሙስሊሞች ሁሉ ሀዲስ አጥባቂ ነበርኩ (ኦሳማ ቢን ላደን ከእነርሱ አንዱ ነበር)። በጣም አክራሪ ናቸው፥ እኔም እንደዛ ነበርኩ።
የመንግስተ ሰማያት ብቸኛው መንገድ እስልምና መሆኑን ተምሬ ነበር። “ይህንን ካደረግህ ይህንን እና ያንን በረከቶች በገነት ታገኛለህ” እና “ያንን ካደረግህ ይህንን እና ያንን በረከቶች በገነት ታገኛለህ” ተብሎ ተነግሮኛል። ለእስልምና ሃይማኖት አክራሪ ሆንኩ።
የማደርገው ነገር ትክክል ነው የሚል እምነት ነበረኝ፣ እናም ትክክል ከሆነ ታዲያ የበለጠ በጥልቀት መመርመር ውስጥ ምንም አደጋ የለውም ብዬ አሰብኩ። ስለ ነቢያት በቁርአን እና በሐዲስ አንብቤ ነበር፥ ግን ከሌሎቹ በበለጠ በእውነት የነካኝ ብቸኛ ኢየሱስ ክርስቶስ ነበር። ክርስቲያኖች ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ ነው ብለው እንደሚያምኑ ተረዳሁ። ለምን እንዲህ እንደሚያምኑ በጣም ገርመኝ። ኢየሱስ ክርስቶስን የበለጠ መፈለግ ጀመርኩ። አብሮኝ የሚያጠና አንድ ክርስቲያን ጓደኛ ነበረኝ። አንድ ቀን የእርሱን መጽሐፍ ቅዱስ መውሰድ እችል እንደሆነ ጠየቅኩት። በመገረም “ይቅርታ፣ መውሰድ አትችልም” አለኝ። ማንም ሊያውቀው እንደማይችል አረጋግኩለት። “በእኔ እና በአንተ መካከል ይቀራል” አልኩት። አባቴ ግን መጽሐፍ ቅዱስ እንዳነበብኩና በቤታችን ውስጥ እንዳለ አወቀ። አባቴ በጣም ተቆጣ፤ አንድ ክርስቲያን ጓደኛ ብቻ እንዳለኝም ያውቅ ነበር። ስለዚህ ከአጎቴ ጋር ወደዚህ ጓደኛዬ ቤት ወስዶኝ እንዲህ ሲል አስጠነቀቃቸው “ይህንን ድጋሚ ካደረጋችሁ እና ክርስትናን ለሙስሊም ልጄ ለመስበክ ከሞከራችሁ ብዙ መከራ ይደርስባችኋል፤ ታውቁታላችሁም። ለእስላማዊ ፖሊስ (ሙታዋ) አመለክታለሁ እናም ከዚህ ሀገር እስከ መጨረሻው ልትባረሩ ትችላላችሁ።” ተጨንቄ ነበር። በጓደኛዬ ቤተሰቦች ላይ ይህን ማድረግ አልነበረብኝም።
እንደ ከዚህ በፊቱ በቀን አምስት ጊዜ እና አንድ ጊዜ በመስጊድ ውስጥ እንድሰግድ አባቴ አስጠነቀቀኝ፣ አጎቴም አስጠነቀቀኝ። መሄዴን ቀጠልኩ፣ እና ብዙ ጊዜ በመስጊድ ውስጥ ማንም በማይኖርበት ጊዜ አለቅስና እግዚአብሔርን “ይህ ኢየሱስ ማን ነው? እና አንተ ማን ነህ?” ብዬ እንዲያሳየኝ እጠይቃለሁ። ብዙውን ጊዜ የሶላቱ ኢማም (መሪ) በአረብኛ ሲጸልይ (በአረብኛ ብቻ መጸለይ ግዴታ ስለሆነ)፣ እርሱ ለሚናገረው ብዙም ትኩረት አልሰጥም ነበር። አንድ ቀን በመስጂድ ውስጥ፣ የዙሃር ሶላት (የእኩለ ቀን ሶላት) ወቅት እሰግድ ነበር። በዚያን ጊዜ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ እያሰብኩ አልነበረም። በጸሎት ደፍተን በምንሰግድበት ወለል ላይ የአንድ መልከመልካም ሰው ምስል አየሁ። ደነገጥኩ። ከዚህ በፊት እንደዚህ ያለ ነገር በፍፁም አይቼ አላውቅም ነበር። በውሃ ላይ ያለ ዓይነት ምስል ነበር። ይህ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሆነ በውስጤ ሰማሁ። ይህ ጌታ ነው!
ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ የማወቅ ረሃቤ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ሄደ።
መጽሐፍ ቅዱስ አልነበረኝም። አንድ ቀን ከጓደኛዬ ጋር በሱቆች ውስጥ እያለፍኩ ወደ ኢንተርኔት ካፌ ደረስን። በyahoo.com ላይ ነበርኩ እና በአእምሮዬ ውስጥ አንድ ሀሳብ መጣ። “ኢየሱስ ማን ነው?” ብለህ ፈልግ የሚል። አደረግሁት፥ እናም ብዙ ድረ ገጾችንም አገኘሁ። እዚያ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ መፈለግ በመቻሌ በጣም ተገረምኩ።
አንድ ድረ ገጽ ስለ ኢየሱስ ማንነት እና በብሉይ ኪዳን ስለ እርሱ ስለ ተነገሩ ትንቢቶች እና በአዲስ ኪዳን ውስጥ ምን ያህል በሚያስደንቅ ሁኔታ እንደተፈጸሙ በጣም ጥሩ መረጃዎችን ሰጠኝ።
በጣም ተገረምኩ። ብዙ ጊዜ ወደዚህ ድረ ገጽ መምጣትን ቀጠልኩ። አንድ ቀን ኢየሱስን ለመሞከር አሰብኩ እና በድረ ገፁ ላይ ያለውን የድነት ፀሎት ጸለይኩ።
ወደ መስጊድ ለመጸለይ ስሄድም ያንኑ የኢየሱስ ክርስቶስን ምስል በተደጋጋሚ አይ ነበር። አንድ ቀን አቋራጭ መንገድ በመጠቀም ወደ ገበያ እየተጓዝኩ ነበር። ትንሽ ገለልተኛ አካባቢ ነበር። በዚያ የሚያልፉ ብዙ ሰዎች አይደሉም። እየተራመድኩኝ እያደረኩ ያለሁት ነገር ትክክል ነው? ክርስቲያን ወይስ ሙስሊም መሆን አለብኝ? እያልኩ እያሰብኩ እና እግዚአብሔርን እየጠየኩ ነበር። ከኋላዬ “ልጄ በትክክለኛው መንገድ ላይ ነህ” የሚል ድምፅ ሰማሁ። እንደገና ተገረምኩ። እንደዚህ አይነት ነገሮች አጋጥመውኝ አያውቁም።
ግን ባለፍኩባቸው ነገሮች ሁሉ ብዙ ነገሮችን የሚናገረውን መጽሐፍ ቅዱስን ሳውቅ የበለጠ ደስተኛ ሆንኩ። ለምሳሌ እንዲህ ይላል
"ወደ ቀኝም ሆነ ወደ ግራ ዘወር ብትል ጆሮህ ከኋላህ፣ “መንገዱ ይህ ነው፤ በእርሱ ሂድ” የሚል ድምፅ ይሰማል።"1
እንዲህም ይላል፥
"ለእናንተ ያለኝን ዕቅድ እኔ ዐውቃለሁ” ይላል እግዚአብሔር፤ “ዕቅዱም ፍጻሜው ያማረና ተስፋ የሚሰጥ፣ እናንተንም የሚጠቅም እንጂ የሚጐዳ አይደለም። እናንተም ትጠሩኛላችሁ፤ ቀርባችሁ ወደ እኔ ትጸልያላችሁ፤ እኔም እሰማችኋለሁ። እናንተ ትፈልጉኛላችሁ፣ በፍጹም ልባችሁም ከፈለጋችሁኝ ታገኙኛላችሁ፤"2
እግዚአብሔር ለእኔ ታማኝ ሆኖልኛል!
መጽሐፍ ቅዱስን ካልመረመርኩና ለሕይወቴ የእግዚአብሔርን መመሪያ ካልጠየቅኩ የት እደርስ ነበር? የመጽሐፍ ቅዱሱ እግዚአብሔር ከማንም በላይ ይመልሳል! እውነታው ይህ ነው!
በቁርአን ውስጥ አንዳንድ መገለጦች እንደተሰረዙ ወይም እንደተረሱ ይናገራል።3
ያ ማለት ምን ማለት ነው? በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የዚህ ተቃራኒ አለ።
በኦሪት ዘኁልቍ 23፥19 እንዲህ ይላል፣
"ይዋሽ ዘንድ እግዚአብሔር ሰው አይደለም፤ ይጸጸትም ዘንድ የሰው ልጅ አይደለም፤"
በዛቡር (መዝሙረ ዳዊት 31:5) ደግሞ እንዲህ ይላል፥
"መንፈሴን በእጅህ ዐደራ እሰጣለሁ፤ እግዚአብሔር የእውነት አምላክ ሆይ፤ አንተ ተቤዠኝ።"
እና ኢንጂል (ዮሐንስ ወንጌል) 17:17 እንዲህ ይላል፤
"ቃልህ እውነት ነው፤ በእውነትህ ቀድሳቸው።"
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እግዚአብሔር ይዋሻል ወይም ቃሎቹን ለውጦ ሰዎችን ወደ ስሕተት እንደሚወስድ የሚገልጽ አንድም ጥቅስ አላገኘሁም።
በቁርአን ውስጥ በሁሉም ነቢያት እና በተገለጡት የአምላክ መጻሕፍት፣ በኦሪት፣ በዛቡር፣ በኢንጂል እና ዳንኤልን ጨምሮ እንድናምን ተነግሮናል። የእግዚአብሔር ቃሎች ናቸው ብለን በእነርሱ ካላመንን እኛ ሙስሊሞች አይደለንም። መጽሐፍ ቅዱስን ከዚህ ምድር ለማጥፋት ብዙ እርምጃዎች እና ጥረቶች ተወስደዋል ግን በፍፁም አልተሳካላቸውም። ያ የገለጠው እግዚአብሔር እንዴት መጠበቅ እንዳለበት በደንብ እንደሚያውቅ ያረጋግጣል። መጽሐፍ ቅዱስ ተለውጧል የሚሉትን ሁሉ በማስረጃ እንዲያስረዱኝ እገዳደራቸዋለሁ። በመቶዎች የሚቆጠሩ ሳይንቲስቶች አጥንተውት ግልፅነቱን እና የተጻፈውን አረጋግጠዋል።
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተነገሩት ትንቢቶች ዛሬ እየተፈጸሙ ናቸው። እነዚህ በጣም አስደናቂ ከሆኑት ነገሮች መካከል የዚህ መጽሐፍ ደራሲ ማን እንደሆነ ያረጋግጣሉ። የዚህ ዓለም ፈጣሪ ነገ እና በሚቀጥሉት ቀናት የሚሆነውን ያውቃል። እርሱ እንደ ሳይኪክ አይተነብየውም ነገር ግን ያውቀዋል!
በኢየሱስ እና በመሐመድ መካከል ያለውን ልዩነት መረዳቱም አስገራሚ ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንዲህ ይላል፡
"በመጀመሪያ ቃል ነበረ፤ ቃልም ከእግዚአብሔር ጋር ነበረ፤ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ!"4
ለምንድነው ኢየሱስ ክርስቶስ የምስራች፣ በአላህ ዘንድ ቅርብ የሆነ የእግዚአብሔር ቃል ተብሎ የተጠራው፣ ነገር ግን ስለ መሐመድ እንደዚህ የተጠቀሰው ነገር የሌለው?
ደግሞም፣ ኢየሱስ ክርስቶስ እንከን የለሽ እና ያለ ኃጢአት ሆኖ፣ ነገር ግን በቁርአን ውስጥ ብዙ ጊዜ መሐመድ ከኃጢአቶቹ ንስሃ እንዲገባ ማሳሰቢያ ተሰጥቶታል። ቁርአንን በመረዳት የሚያነብ ማንኛውም ሙስሊም በደንብ ያውቀዋል።
መጽሐፍ ቅዱስም ኢየሱስ ክርስቶስ ተአምራትን እንዳደረገ እና ከእግዚአብሔር በስተቀር ማንም ሊያደርጋቸው የማይችላቸውን ሌሎች ብዙ ነገሮችን እንዳደረገ ይናገራል ... ለሞት ሕይወት መስጠትን፣ በሽተኞችን መፈወስን የመሳሰሉትን።
መሐመድ ለምን ያንን አላደረገም? በዘመኑ ብዙ ሰዎች ተአምራትን ቢጠይቁም ፈቃደኛ አልሆነም። አንድ ተአምር በቁርአን ውስጥ - ጨረቃን ለሁለት እንደከፈላት ተመዝግቧል። ያ ለሰው ልጅ ምን ጥቅም አስገኝቷል?
ኢየሱስ ክርስቶስ ከመወለዱ በፊት እንከን በሌለው ልጅ ከድንግል በክብር እንደሚወለድ ለማወጅ መላእክት ተልከው ነበር። መሐመድ ግን በእስልምና ውስጥ ከነቢያት ሁሉ የላቀ ሆኖ ያን ክብር አልነበረውም። ለምን ስለ መሐመድ ተመሳሳይ ነገር አልተባለም?
እግዚአብሔር በእውነት ድንግል እንድትወልድ ማድረግ ከቻለ ታዲያ እርሱን ልጁ ብሎ መጥራት ለምን ይከብደዋል?
ቁርአን ለሰው ልጅ መገለጥ እና ምህረት እንደሚኖር ይናገራል።5 ሙስሊሞች ለሰው ልጆች ስለ
በኢንጂልን (በወንጌል) ውስጥ በማርቆስ 10፥46-47 አንድ ዓይነ ስውር ሰው ወደ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ጮኸ፡
“ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ ከብዙ ሕዝብ ጋር ከኢያሪኮ ሲወጡ ዐይነ ስውሩ የጤሜዎስ ልጅ በርጤሜዎስ በመንገድ ዳር ተቀምጦ ይለምን ነበር። እርሱም የናዝሬቱ ኢየሱስ መሆኑን በሰማ ጊዜ፣ “የዳዊት ልጅ፣ ኢየሱስ ሆይ፤ ማረኝ!” እያለ ይጮኽ ጀመር።"
በአዲስ ኪዳን ውስጥም፡
"ወደ ዘላለም ሕይወት የሚያደርሳችሁን የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ምሕረት ስትጠባበቁ ሳለ፣ በእግዚአብሔር ፍቅር ራሳችሁን ጠብቁ።"6
"የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባትና አምላክ ይባረክ፤ እርሱ ከታላቅ ምሕረቱ የተነሣ በኢየሱስ ክርስቶስ ከሞት መነሣት ምክንያት ለሕያው ተስፋ በሚሆን አዲስ ልደት፣ 4እንዲሁም በሰማይ ለማይጠፋ፣ ለማይበላሽና ለማይለወጥ ርስት እንደ ገና ወለደን።"7
ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በጊዜው ለነበሩ ሰዎች ወይም በአከባቢው ለነበሩ ሰዎች ብቻ የተሰጠ ምህረት አልነበረም። ከሞሐመድ በኋላም ቢሆን እግዚአብሔር ለሁሉም ሰው ምሕረትን ሰጠ።
እኛ ኃጢአተኞች እንደሆንን እና ከጌታ የራቅን እንደሆንን ከመጽሐፍ ቅዱስ እናውቃለን። ከጌታ ጋር እኛን ለማስታረቅ ብቸኛው መንገዳችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፣ ምክንያቱም እርሱ ኃጢአት የሌለበት ነበር፥ ስለ እኛም ኃጢአት ሆኗልና። ኃጢአቶቻችን በእርሱ ላይ ተደረጉ።
ኢየሱስ ክርስቶስ ኃጢአታችንን ተሸክሞ ለእኛ ኃጢአት ሆነ። በኢንጂል (በወንጌል) እንዲህ ይላል
"ወንድ ልጅ ትወልዳለች፤ ስሙንም ኢየሱስ ብለህ ትጠራዋለህ፤ ሕዝቡን ከኀጢአታቸው ያድናቸዋልና።"8
ለሌሎች ብዙ ሰዎች ከኃጢአቶች እንዲድኑ እንደሚፈልግ በማመልከት “ኃጢአትህ ተሰረየችልህ” ብሏል! እርሱ ኃጢአታቸውን ተሸከመ!
እንዲሁም ከአዲስ ኪዳን፡
"እኛ በእርሱ (በኢየሱስ) ሆነን የእግዚአብሔር ጽድቅ እንድንሆን፣ ኀጢአት የሌለበትን እርሱን (ኢየሱስን) እግዚአብሔር ስለ እኛ ኀጢአት አደረገው።"9
ብዙ ሰዎች የእግዚአብሔርን ምህረት በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ አግኝተው ተለውጠዋል። አንዱ እኔ ነኝ። ብዙዎች ተአምራትን፣ ሥልጣንን፣ እውነትን በተሳሳተ ስፍራ ብቻ ብቻ ይፈልጋሉ፣ ወደ ወደ እግዚአብሔር የሚወስደውን መንገድ የሚያውቅ ብቻ ሳይሆን ራሱ ብቸኛው መንገድ የሆነውን እርሱን እስካገኘው ድረስም እኔም እንደዛው ነበርኩ። በኢየሱስ ቃላት አድምጡ፡
“ኢየሱስም እንዲህ አለው፤ “መንገዱ እኔ ነኝ፤ እውነትና ሕይወትም እኔው ነኝ፤ በእኔ በኩል ካልሆነ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም። እኔን ብታውቁኝ ኖሮ አባቴንም ባወቃችሁት ነበር። ከአሁን ጀምሮ ግን ታውቁታላችሁ፤ አይታችሁታልም።””10
መሐመድ እና ሙስሊሞች መመሪያ ለማግኘት በትጋት ጸሎታቸው በየቀኑ ብዙ ጊዜ ይጸልዩ ነበር፣ እናም በሚገርም ሁኔታ የመጨረሻው እና ትልቁ የእስልምና ነቢይ እስከ ህይወቱ መጨረሻ ድረስ መጸለዩን ቀጠለ።11
መሐመድ ቀጥተኛውን መንገድ ላይ ነበርን? እስልምና ቀጥተኛው መንገድ ነውን? ሁሉም ሙስሊሞች ወደ ሰማይ ለመሄድ የሚያደርጉት ነገር በእርግጥ እውነት መሆኑን ራሳቸውን እንዲጠይቁ አበረታታለሁ።
መንግስተ ሰማይ በእግዚአብሔር ምህረት እና ጸጋ ብቻ እንጂ በስራችን ልንገዛት የምንችላት ቦታ ናት ብዬ አላምንም። እግዚአብሔር በየቀኑ በእያንዳንዳችን ውስጥ የበለጠ ረሃብ እንዲጨምር እና ለመንፈሳዊ ምግባችን እና መዳናችን ወደ እርሱ ዘወር እንድንል እጸልያለሁ! ከመቼውም ጊዜ በበለጠ በጣም ቀላል ተደርጓል። በትህትና ልብ ወደ እርሱ ኑ። ፊቱን ፈልጉ እና በእቅፉ ውስጥ ራሳችሁን አግኙ!
በክርስቶስ አዲስ ፍጥረት ሆነናል። የተፃፈው ከረጅም ጊዜ በፊት ነበር፣ ግን ዛሬም እውነት ነው! የፈጠረን አእምሯችን እና ሀሳባችን እንዴት እንደሚለወጡ እና ያንን የጎደለውን ክፍተት እንዴት እንደሚሞላ እና ወደ እርሱ ብቸኛ መንገድ በሆነው በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል መንፈሳዊ ህይወታችንን እንደገና እንዴት እንደ ሚሞላ ያውቃል!
ስለዚህ ወንድሞቼ እና እህቶቼ አስደናቂ ፍቅርን ለመቀበል ልባችሁን እና አዕምሮአችሁን ክፈቱ። ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን በሕይወታችሁ እንዲገባ ፍቀዱ እና ቀጥሎ የሚሆነውን ተመልከቱ። በምድር ላይ ትልቁ ጉዞ ይጀምራል። በችግር ውስጥ በሆንኩበት ጊዜ ሁሉ እርሱ ከእኔ ጋር ነበር፤ ማንም ሊያደርገው ከሚችለው በላይ አፅናናኝ። እርሱ ለዘላለም ሕያው እንደሆነ እና በጣም እንደሚወደኝ አሳይቶኛል።
ልጁን ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን ለእኔ እና ለሁላችን እንዲሞት ስለላከው እና ወደ እርሱ ለመድረስ አስደናቂውን እና የከበረውን ድልድይ ስላደረገ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ! ከእርሱ ጋር ግንኙነት እንዴት እንደምትጀምሩ ለመረዳት ይህንን ጽሁፍ ያንብቡ - ከጭፍን እምነት በላይ
► | ከእግዚአብሔር ጋር ግንኙነትን እንዴት እንደምትጀምር |
► | ጥያቄ አለኝ |
የግርጌ ማስታወሻ: (1) ኢሳይያስ 30:21 (2) ኤርምያስ 29:11-13 (3) ሱራ አል-በቀራህ 2፥106 (4) (ኢንጂል) ዮሐንስ 1:1 (5) ሱራ መሪየም 21 (6) ይሁዳ 21 (7) 1ኛ ጴጥሮስ 1፥3 (8) ኢንጂል (ወንጌል) ማቴዎስ 1፥21 (9) 2ኛ ቆሮንቶስ 5፥21 (10) ዮሐንስ 14፥6-7 (11) ሱራ አል-ፋቲሐህ 3