እስቲ አንድ መዶሻ እንውሰድ ፣ ይህ መዶሻ ምስማር እንዲመታ ታስቦ ነው የተሰራው፤ መዶሻ የተሰራበት ዓላማ ይኸው ነው። ለምሳሌ መዶሻው ለጊዜው ሳንጠቀምበት ፣ በዕቃ ማስቀመጫ ሳጥን ውስጥ እናስቀምጠዋለን። በዚህ ጊዜ መዶሻው ምነው ሳጥን ውስጥ ታስሬ ተቀመጥኩ ? መዶሻው ምንም አይመስለውም፡፡
ይኸው መዶሻ ሕሊና ቢኖረው ኖሮ በውስጡ አንድ ነገር ያስባል ። ዕለት በዕለት ያለምንም ሥራ በሳጥን ውስጥ ታሽጎ መቀመጡ ያሳስበዋል። በውስጡ ምንም ያህል የሚያሳስበው ጉዳይ ቢሆንም፣ ለምን ታሸጎ እንደተቀመጠ ምክንያቱን ሊደርስበት አይችልም፤ አንድ ችግር ሊኖር ይችላል። ችግሩን ግን ምን እንደሆን ሊያውቅ አይችልም።
ከዕለታት አንድ ቀን መዶሻውን አንድ ሰው ታሽጎ ከተቀመጠበት ሳጥን ውስጥ አውጥቶት ፣ ለማገዶ የሚሆን እንጨት ከዛፍ ላይ ቅርንጫፎችን ይቆርጥበት ጀመር ፤- ይህን ተግባር መዶሻው በጣም ወደደው። በዕለቱ መጨረሻ ላይ ያን ያህል ደስታው ወሰን ያጣው መዶሻ ፣ እንደ ጅማሬው ደስታው አልቀጠለም፤ ከፋው። ቅርንጫፎችን መጨፍጨፍ ለጊዜ ማሳለፊያና ለቧልት የሚያደርገው ክዋኔ እንጂ፥ ከተፈጠረበት ዓላማ ጋር የሚሄድ አልነበረምና አሁንም አንድ ነገር የጎደለ ነገር እንዳለ ይሰማው ነበር።
በሚቀጥለውም ቀን ቀድሞ እንደሚያደርገው ቀጠለ። አንድ እግሩ ለተሰበረ ጠረቤዛ መቆሚያ ይሆን ዘንድ ድንጋይ ጠርቦ ለጠረቤዛው እግር ሰራለት ፤ አሁንም በዚህ ሥራው አልተደሰተም። የተሻለ ስራ ተመኘ ስራ ተመኘ ሥራው በዙሪያው የሚገኙትን መደብደብ ያለባቸውን ነገሮች መደብደብ፥ መጨፍጨፍ፥ መፈረካከስና መጠራረብ ፈለገ ስለዚህ አንድ ነገር ተረድቷል። እስካሁን ያከናወናቸው ተግባራት ከቶም ቢሆን ርካታን የሚሰጡት እንዳልነበሩ ለመገንዘብ ጊዜ አልፈጀበትም። ይብዛም ይነስ በሥራ ላይ የተሰማራ ቢሆንም በአገልግሎቱ ግን የእርካታ እጦት እያንገላታው ቆየ።
እንደገናም ከዕለታት በአንዱ ቀን፥ አንድ ሰው መጣና ይዞት ሄዶ ምስማር ይመታበት ጀመር። ወዲያውኑ ከመዶሻው ሕይወት ውስጥ የእሳት ብልጭታ ተፈጠረ። ያን ጊዜ እርሱ ለምን ዓላማ እንደተፈጠረ ገባው። ምስማርን ለመምታት ነበር የተፈጠረው። በዚህ ጊዜ በእርጋታ ሆኖ ከዚህ በፊት ሲመታቸው የነበሩትን ነገሮች ከአሁኑ ጋር እያነጻጸረ ነገሮችን ማሰላሰል ጀመረ። ያ መዶሻ ሕይወቱን ሙሉ ሲፈልገው የነበረውን የተፈጠረለትን ዓላማ አገኘና ተረዳው።
እኛ በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠርነው ከእግዚአብሔር ጋር ገንኙነት እንዲኖረን ነው። በዚህች ምድር ላይ ነፍሳችንን የሚያረካው፣ ብቸኛውና ዘላቂው መፍትሄ ከእግዚአብሔር ጋር ግንኙነት አንዲኖረን ማድረግ ነው። የሚገርመው ግን እግዚአብሔርን እስከምናውቀው ድረስ ሕይወታችን የተፈጠረችበትን ዓላማ በመፈለግ ሂደት ውስጥ እጅግ በጣም አስገራሚ በሆኑ ልምምዶች ውስጥ እንደምናልፍ ሳይታለም የተፈታ ነው። ልክ መዶሻው የተፈጠረበትን ምስማር የመምታት ዓላማ ዕድሉን ከማግኘቱ በፊት እንዳለፋቸው ሂደቶች እኛም የተፈጠርንበትን ዓላማ ሳናውቅና ሳናገኝ እንዲሁ በመባዘን እንዳለፍን ግልጽ ነው። እጅግ በጣም የተከበሩ በምንላቸው ዓላማዎች ዙሪያ ራሳችንን አግኝተን ሊሆን ይችላል፣ ቢሆንም የተከበሩ ዓላማዎች መስለውን ቢታዩንም ከተፈጠርንበት ዓላማ ጋር የማይሄዱና ፈጽሞ እርካታን የማናገኘባቸው ሊሆኑ ይችላሉ። ቅዱስ አውግስጦስ ይህን ዕውነታ እንዲህ ብሎ በድንቅ አገላለጽ አቅርቦታል፤ «እግዚአብሔር ሆይ አንተ ለራስህ ክብር ፈጠርኸን፤ ስለዚህ ነፍሳችን አንተን አግኝታ እስከምታርፍ ጊዜ ድረስ መቼም ቢሆን እፎይ አትልም፡፡» አለ።
ከእግዚአብሔር ጋር ካለን ግንኙነት በስተቀር የነፍሳችንን ጥም የሚያረካ ምንም ነገር የለም። ይህንን ዕውነት አስመልክቶ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲህ አለ፡- «የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ፤ ወደ እኔ የሚመጣ ከቶ አይራብም፤ በእኔ የሚያምንም ሁልጊዜ ከቶ አይጠማም።» ዮሐ .6፥35 እግዚአብሔርን እስክናውቀውና ወደ እርሱ እስክንመጣ ድረስ ነፍሳችን በታላቅ ርሃብና ጥማት ውስጥ ሆና ትንገላታለች። ለነፍሳችን እርካታ ስንል መብል ነው የምንለውንና መጠጥ ነው ብለን የተቀበልነውን ሁሉ እንሞክራለን፤ የዚህን ጊዜ መዶሻው የማንነቱን ዓላማ እስከሚያውቅ ድረስ በተለያዩ ሙከራዎች አልፎ ምንም ርካታን ማግኘት እንዳልቻለ ሁሉ እኛም ፈጽሞ እንደማንረካ የታወቀ ነው። ባዶነታችንን ምን እንደሚሞላና የነፍሳችን እርካታ ምንጩ ምን እንደሆነ በትክክል እስክናውቅ ድረስ እንደባዘንን እንኖራለን። ኮሪ ቴምቡ የተባለች አንዲት አይሁዳዊት ክርስቲያን በናዚ የማጎርያ ካምፕ ውስጥ ሆና እንኳን ሆና እግዚአብሄር የእርካታዋ ምንጭ ሆኖ አግኝታዋለች። ከዚያ በኋላ፡- «የደስታችን ምንጭና መሠረት እንዲሁም ማንነታችን በእግዚአብሔር አምላክ በክርስቶስ በኩል እንደተሠራ ማወቃችን ነበር። . በእግዚአብሔር ፍቅር ዕምነት ነበረን። አለታችን ጥቅጥቅ ካለው ጨለማ ይልቅ ጠንካራ ነው።. . . » አለች።
ብዙዉን ጊዜ እግዚአብሔርን ከውስጣችን ስናወጣ፣ ዕርካታን እናገኝበታለን ብለን የማንሞክረው ነገር የለም። ነገር ግን ከቶም ቢሆን ምንም የሚያረካ ነገር አናገኝም። በቃን እስከምንል ድረስ እንበላለን እንጠጣለን፣ አሁንም ደግመን እንበላለን እንጠጣለን። በተሳሳተ አሰተሳሰብ የሞከርናቸውን ነገሮች ሁሉ መጠናቸውን ጨምረን ብዙ መውሰድ ምናልባት እርካታን ይሰጠናል ብለን እንገምታለን። ግን ለችግራችን ፈጽሞ መፍትሄ አናገኝም። ስለዚህ ጥማታችንና ርሃባችንን ሳናረካ እንደው እንደባዘንንና እንደተቅበዘበቅን እንቀራለን።
የኛ ትልቁ ፍላጎትና ጥማት እግዚአብሔርን ማወቅ ነው። ከዚያም ከእርሱ ጋር ግንኙትን መመስረት ነው። ለምን? ምክንያቱም የተፈጠርነው ለዚሁ ዓላማ ነውና። አሰካሁን ምስማሩን አልመታችሁም?
► | ከእግዚአብሔር ጋር ግንኙነትን እንዴት እንደምትጀምር |
► | ጥያቄ አለኝ |