×
ፈልግ
ስለህይወት እና ስለእግዚአብሄር በነፃነት
 ጥያቄ የሚጠይቁበት ድረገጽ
የህይወት ጥያቄዎች

ሕይወት ለምን እንዲህ ከባድ ሆነ?

“ለምን?” ሕይወት ሲከብድ፣ ሰላም ማግኘት የሚቻልበት መንገድ ይኖር ይሆን?

WhatsApp Share Facebook Share Twitter Share Share by Email More PDF

ሰዎች ለምን በካንሰር ይሰቃያሉ? ከተሞችን እንዳልነበሩ የሚያደርጉ ርዕደ መሬቶች ለምን ይከሰታሉ? የቤተሰባቸውን ጉሮሮ ለመድፈን ያህል ብቻ ሰዎች ሌት ተቀን ለምን በሥራ ይባክናሉ?

እንዲያውም በደመነፍስ ሳናስተውለው፣ ደግመን ደጋግመን በውስጣችን እነዚህን ጥያቄዎች ማብሰልሰላችን አይቀርም:: በአፋችን አውጥተን ግን ስንጠይቃቸው አይሰሙም፡፡ የህይወት ትንቅንቅ ለማሸነፍ ደፋ ቀና ስንልና መተንፈሻ ስናጣ ቆም ብለን ለምን? የምንለው ከስንት አንድ ጊዜ ነው፡፡

ወደድንም ጠላንም ነቃ የሚያደርገን አንድ ነገር ይከሰታል፡፡ ወላጆቻችን ይፋታሉ፡፡ ልጃገረዲቱም በጉልበተኛው ትደፈራለች፡ ከዘመዶቻችን አንዱ ካንሰር ይከሰትበታል ይህም ሁኔታ ያባንነናል ብዙም ሳንቆይ ግን ሁሉንም እንዘነጋለን፡፡ ይህም የሚሆነው ሌላ አሰቃቂ ነገር እስኪመጣ የሚያጋጥም ነገር እስኪከሰት ነው፡፡ ያን ጊዜ ቆም ብለን እዚሀጋ እንድ ትክክል ያልሆነ ነገር አለ፣ በእውነት በእውነት አንድ የተሳሳተ ነገር አለ ብለን ማሰብ እንጀምራለን፡፡ ሕይወት ሊሆን የሚገባው እንዲህ አልነበረም እንላለን፡፡ ታዲያ ክፉ ነገሮች ለምን ይከሰታሉ? ይህች ዓለም የተሻለ ስፍራ የማትሆነውስ ለምንድነው? በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ለምን ለተሰኘው ጥያቄ መልስ አለ፡፡ ይህ መልስ ግን ብዙዎች ሲሰሙት የሚወዱት መልስ አይደለም፡፡ ዓለም አሁን የሆነችውን የሆነችው እኛ ልትሆንልን የምትሻው ዓይነት ስለነበረች ነው፡፡

ምን አይነት እንቆቅልሽ ?

ዓለም አሁን ከሆነችው የተለየች እንድትሆን ማድረግ የሚችል ምንድነው ማንስ ነው? ሕይወት በሁሉም ዘመን ለሁሉም ሰው ስቃይ አልባ እንድትሆን ማድረግ የሚችል ምንድነው ማንስነው?

እግዚአብሔር ይችላል እግዚአብሔር ያንን ማድረግ ይችላል፡፡ ግን አላደረገም ቢያንስ አሁን አላደረገውም፡፡ ይህም ስለሆነ በእርሱ ላይ እንቆጣለን፡፡ ስለዚህም “እግዚአብሔር ሁሉን ቻይ እና ሁሉን አፍቃሪ አይደለም፡፡ ሆኖ ቢሆን ኖሮ ዓለም አሁን እንደምናያት ባልሆነች ነበር!” እንላለን፡፡

ይህንንም የምንለው ቁጣችንን አይቶ እግዚአብሔር በጉዳዩ ላይ ያለውን አሳብ ይለውጣል በሚል ተስፋ ነው፡፡ ተስፋችንም የእርሱን ወንጀል ባበዛነው ቁጥር ነገሮችን የሚያከናውንበትን አሰራሩን ይለውጣል የሚል ነው፡፡

እርሱ ግን ወይ ፍንክች! ለምን ግን?

እግዚአብሔር ግን አይለወጥም… ነገሮችንም አሁን አይለውጥም … ምክንያቱም እኛ የምንጠይቀውን ነገር ሰጥቶናልና እርሱ እንደሌለና አላስፈላጊ እንደሆነ የቆጠርንበትንና የምንኖርበትን ዓለም ሰጥቶናል፡፡

የአዳምንና የሔዋንን ታሪክ ታስታውሳላችሁ? “እንዳይበሉ የተከለከሉትን ፍሬ; በሉ፡፡ ፍሬዋም እግዚአብሔር የተናገራቸውንና የሰጣቸውን ቸል ብለው ሕይወትን ከእግዚአብሔር ውጪ ለመምራት ማመጻቸውን የሚገልጽ ነው፡፡ አዳምና ሔዋን ይህንን ሲያደርጉ ከእግዚአብሔር ተለይተው እንደ እግዚአብሔር የመሆን ቀቢፀ ተስፋ በውስጣቸው ይዘው ነው፡፡ ከእግዚአብሔር ከራሱ የተሻለ ለመኖር ትርጉም የሚሰጥ አንድ ነገር አለ፣ ከእግዚአብሔር በግል የቀረበ ወዳጅነት ከማድረግ የተሸለ ዋጋ የሚሰጠው ሌላ ነገር አለ በሚል አስተሳሰብ ተውጠው ነበር፡፡ ዛሬ የምናየው የዓለም ስርአት… የሚታየው ዝብርቅርቅ ሁሉ… የእነርሱ የምርጫ ውጤት ነው፡፡

የእነርሱ ታሪክ፣ የእኛ የሁላችን ታሪክ ነው፡ አይደለምን? ምንም እንኳን ለሰው በሚሰማ ድምፅ ባይናገረውም ሁሉም በልቡ እግዚአብሔር፣ ይህችን እንኳን ለብቻዬም እዘልቅበታለሁ፡፡(ግን ስለስጦታህ አመሰግንሃለሁ፡፡)

እኛ ሁላችንም ሕይወትን ያለእግዚአብሐየር መምራት እንሞክራለን፡፡ ይህንን ለምን እናደርጋለን? ምናልባት ሁላችንም ከእግዚአብሔር የተሸለ፣ የተመረጠ አንድ ሌላ ነገር አለ የሚለውን እሳቤ ሸምተነው ይሆንን? ለተለያዩ ሰዎች የተለያየ ነገር ሊሆን ይችላል፣ እሳቤው ግን ያው ነው፡፡ በሕይወት ውስጥ ዋናው እግዚአብሔር አይደለም፡፡ እንዲያውም እርሱ ምንም ሳያስፈልገኝ መሆን የምሻውን አሁኑኑ ላደርገው እችላለሁ የሚል እሳቤ ነው፡፡

ለዚህ እሳቤ የእግዚአብሔር ምላሽ ምንድን ነው?

ይሁንላችሁ! ይላል፡፡ በርካታ ሰዎች ሌሎች በሚያደርሱባቸው አሊያም በራሳቸው ምርጫ ከእግዚአብሔር መንገድ ውጪ የሚያከናውኗቸው ተግባራት የሚያመጡባቸውን ስቃዮች ይጎነጫሉ ግድያ፣ መደፈር፣ ስግብግብነት፣ ውሸት/ማጭበርበር፣ ስም ማጥፋት፣ ምንዝርና፣ ጠለፋ(የልጆች ስርቆት) ወ.ዘ.ተ እነዚህ ሁሉ ነገሮች የሚከናወኑት በሕይወታቸው ለእግዚአብሔር ስፍራ በማይሰጡና እንዲገዛቸው ባልፈቀዱለት ሰዎች ውስጥ ነው፡፡ ሕይወትን እነርሱ በመሰላቸው መንገድ ይመሯታል በውጤቱም ብዙዎች ይማቅቃሉ፡፡

እግዚአብሔር ይህንን ሁሉ ነገር እንዴት ያየዋል? በፍጹም አይረካም(ደስ አይሰኝም)፡፡ እግዚአብሔርን ልንረዳው የሚገባን ዛሬም ቢሆን በፍጹም ርህራሄ ወደ እርሱ እንድንመለስና የተሸለ ህይወትን እንድንኖር ለማድረግ የሚናፍቅ አድርገን ነው፡፡ እየሱስ እንዲህ አለ፣ “እናንተ ሸክም የከበዳችሁ ሁሉ ወደ እኔ ኑ፣ እኔም አሳርፋችኅለሁ፡፡” ወደ እርሱ መሄድ የፈለጉት ግን ሁሉም አልነበሩም፡፡ ይህንንም ሁኔታ ሲመለከት “ኦ! ኢየሩሳሌም፣ ኢየሩሳሌም ነብያቶችን የምትገድይ ወደ አንቺ የተላኩትንም ሁሉ በድንጋይ የምትወግሪ ዶሮ ጫጩቶቿን እንደምትሰበስብ ልጆችሽን ሁሉ ልሰበስብ ስንት ጊዜ ወደድሁ አንቺ ግን አላወቅሽም (አልፈቀድሽም)” በማለት ኃዘኑን ገልጧል፡፡ ከዚያም ኢየሱስ ጉዳዩን እኛ ከእርሱ ጋር ሊኖረን ከሚገባው ግንኙነት አንፃር ሲያቀርበው፣ ”እኔ የአለም ብርሃን ነኝ፣ የሚከተለኝም የሕይወት ብርሃን ይሆንለታል እንጂ በጨለማ አይመላለስም” ሲል ገለጠው፡፡

ነገር ግን ሕይወት ዝብርቅርቅ ሲልስ?(ያልተገባ ነገር ሲከሰትባትስ) ከእኛ ውጪ በሆኑ ሰዎች ምክንያት በሕይወታችን ውስጥ አሰቃቂ ሁኔታዎች ሲከሰቱስ? የተጠቃን ሲመስለን (የጥቃት ስሜት ሲሰማን) እግዚአብሔር ራሱ በሌሎች እጅግ ዘግናኝ ሆነ ድርጊት የተፈፀመበት መሆኑን አስታውሱ፡፡ እግዚአብሔር የምናልፍበትን ሁኔታ ከማንም በላይ ይረዳል፡፡

ጌታ ኢየሱስ ስለ እኛ ሲል ያለፈበትንና የታሰበበትን ያህል ስቃይ በምድር ላይ ፍፁም የለም የገዛ ጓደኞቹ ትተውታል፣ በእርሱ የማያምኑ ተሳልቀውበታል፣ ከመሰቀሉ አስቀድሞ ተደብድቦአል ተገርፎአል፣ በመስቀል በሚስማር ተቸንክሮአል፣ አሳፋሪ በሆነ መንገድ በአደባባይ በጣዕር እንዲሞት ተደርጎአል፡፡ የፈጠረን እርሱ ነው፣ ፍጡር ግን ይህንን ሁሉ ስቃይ እንዲያደርስበት ፈቀደ ይህንንም ያደረገው በቅዱሳት መጻሐፍት የተጻፈውን ለመፈጸምና እኛን ከኃጥያት ነፃ ለማውጣት ነው፡፡ የደረሰበት ነገር ኢየሱስን አላስደነቀውም፡፡ ሊመጣበት ያለውን ስቃይ፣ መንገላታቱን ሁሉ ገና በሩቁ ዝርዝሩን ያውቅ ነበር፡፡ ”ኢየሱስም ወደ ኢየሩሳሌም ሲሄድ ሳለ ዐስራ ሁለቱንም ከእርሱ ጋር ወሰዳቸው በመንገድም ሳሉ ; ወደ ኢየሩሳሌም እንሄዳለን፣ የሰው ልጅም ለህፃናት አለቆችና ለፀሐፍት ታልፎ ይሰጣል፣ እነርሱም ሞት ይፈርዱበታል፣ አህዛብም ይሳለቁበትና ያላግጡበት ይስቁበትም ዘንድ አሳልፈው ይሰጡታል በሦስተኛውም ቀን ከሙታን ይነሳል፡፡” እንድ አስፈሪ ነገር እንደሚደርስባችሁ አስቀድሞ ስታውቁ የሚሆንባችሁን እስኪ ገምቱ፡- ኢየሱስ ስሜታዊና ስነ አእምሮአዊ ስቃይን በደንብ ይረዳል፡፡ ኢየሱስ ሊይዙት በሚመጡባት በዚያች ሌሊት ለፀሎት ሲሄድ ጥቂት ወዳጆቹን ከእርሱ ጋር ይዞ ሄደ፡፡ ”ከእርሱም ጋር ጴጥሮስንና ሁለቱን የዘብዲዮስ ልጆች ይዞ በመሄድ ይተክዝና ይጨነቅ ጀመር፤ ነፍሴ እስከ ሞት ድረስ እጅግ አዝናለች ፤ ከእኔ ጋር በመትጋት እዚህ ቆዩ አላቸው ጥቂት አልፍ ብሎ በግንባሩ በመደፋት አባቴ ሆይ ቢቻል ይህ ፅዋ ከእኔ ይለፍ፤ ነገር ግን እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን አንተ ምትፈልገው ይሁን; ብሎ ፀለየ፡፡ ምንም እንኳን በኢየሱስ ዙሪያ ሦስት ወዳጆቹ ቢኖሩም የውስጥ ስቃዩን ጥልቀት አልተረዱለትም፣ ከፀሎት ሲመለስ ያገኛቸው ተኝተው ነበር፡፡ በመከራና በአሰቃቂ ሁኔታ ውስጥ በብቸኝነት ማለፍ ምን እንደሚመስል ኢየሱስ በደንብ ያውቃል፡፡

ዩሐንስ በወንጌሉ ሲጽፍ ነገሩን እንዲህ አጠቃሎታል፣ ”እርሱ በአለም ውስጥ ነበር፤ አለም የተፈጠረው በእርሱ ቢሆንም እንኳ፣ ዓለም አላወቀውም፡፡ ወደራሱ ወገኖች መጣ፤ የገዛ ወገኖቹ ግን አልተቀበሉትም፤ ለተቀበሉትና በስሙ ላመኑት ሁሉ ግን የእግዚአብሔር ልጆች የመሆን መብት ሰጣቸው፡፡; ”በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ህይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስከ መስጠት ድረስ ዓለምን እንዲሁ ወዶአልና” እግዚአብሔር ልጁን ወደ ዓለም የላከው በዓለም ለመድረስ ሳይሆን፣ ዓለምን በእርሱ ለማዳን ነው፡፡;

በዚህ ዓለም እጅግ አሰቃቂ ስቃይና መከራ የመኖሩ ነገር አጠያያቂ አይደለም፡፡ አንዳንዱ የሚደርሰው በራስ ወዳድና ጥላቻ በተሞሉ ሰዎች ምክንያት ነው፡፡ አንዳንዱ ደግሞ በዚህ ሕይወት ውስጥ ማለፍ አስፈራኝ በማለት የሚመጣ ነው፡፡ እግዚአብሐየር ግን እራሱን ሰጥቶናል፡፡ እግዚአብሔር ይህንን በመሰለው መከራ ውስጥ ማለፍን የቀመሰው መሆኑን እንድናውቅ አድርጓል ስለዚህም ስቃያችንንና መሻታችንን ያውቃል፡፡ ኢየሱስ ለደቀመዛሙርቱ ”ሰላምን እተውላችኃለሁ፣ ሰላሜን እሰጣችኃለሁ፤እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጣችሁ አይደለም፡፡ ልባችሁ አይጨነቅ አይፍራም፡፡” እንድንፈራ እንድንጨነቅ የሚያደርገን ከበቂ በላይ የሆነ ምክንያት አለን እግዚአብሔር በፊታችን ካለው ችግር የሚበልጥ ሰላምን ይሰጠናል፡፡ እርሱ እኮ ፈጣሪ የሆነ እግዚአብሔ(አምላክ) ነው፡፡ እርሱ ለዘላለም ይኖራል፡፡ ፍጥረተ አለምን ሁሉ የፈጠረ ከሁሉ ነገር ጀርባ ሆኖ የሚቆጣጠር እርሱ ነው፡፡

ይህን ሁሉ ኃያልነቱን ይዞ፣ እኛን እያንዳንዳችንን በጥልቀት ያውቀናለ፤፣ በጣም ኢምንትና አናሳ የሆኑ ዝርዝር ጉዳዮችን ሁሉ ያውቃል፡፡ በሕይወታችን በሚገጥመን ነገሮች ሁሉ በእርሱ ብንታመን፣ ራሳችንንም በእርሱ ላይ ብናሳርፍ፣ ምንም እንኳን ከፈተናና ከችግሮች ጋር ብንጋፈጥም ያለ አንዳች ጉዳት እርሱ ይዞ ያሳልፈናል፡፡ ኢየሱስ ”በእኔ ሰላም እንዲኖራችሁ፣ ይህንን ነግሬአችኋለሁ፡፡ በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ፤ ነገር ግን አይዞአችሁ፤ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ፡፡” እርሱ የሁሉ የመከራ ቁንጮ በሆነው ሞት ውስጥ አልፎ አሸንፎታል፡፡ በእርሱ የምንታመን ከሆነ በሕይወታችን በሚገጥሙን አስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ እጃችንን ይዞ ይመራናል፣ ወደ ዘላለም ሕይወትም ይወስደናል፡፡

በዚህ ሕይወት ውስጥ ከእግዚአብሔር ጋር ወይም ያለ እርሱ ልንጓዝ እንችላለን፡፡ ”ጻድቅ አባት ሆይ፤ ዓለም ባያውቅህም፣ እኔ አውቅሃለሁ፣ እነዚህም አንተ እንደላክኸኝ ያውቃሉ፡፡ ለእኔ ያለህ ፍቅር በእነርሱ እንደሆነ እኔም በእነርሱ እንድሆን፣ አንተን እንዲያውቁ አድርጌአለሁ፤ እንዲያውቁህም አደርጋለሁ፡፡”

 ከእግዚአብሔር ጋር ግንኙነትን እንዴት እንደምትጀምር
 ጥያቄ አለኝ

ሼር ያድርጉ
WhatsApp Share Facebook Share Twitter Share Share by Email More