×
ፈልግ
ስለህይወት እና ስለእግዚአብሄር በነፃነት
 ጥያቄ የሚጠይቁበት ድረገጽ
FAQ

ኢየሱስ እርሱ አምላክ እንደሆነ ተናግሯልን?

ኢየሱስ እርሱ እግዚአብሔር እንደሆነ ጠቅሷልን? እስቲ ይህን አስደሳች የሆነ ነገር መርምረን እንድረስበት።

WhatsApp Share Facebook Share Twitter Share Share by Email More PDF

ሌሎች ግን እግዚአብሔር አምላክ እንደሆነ አምነው ጽፈዋል።

ሃዋሪያው ጳውሎስ፡ - «እርሱ የማይታይ አምላክ ምሣሌ ነው።» ቆላ. 1፡16
<ሃዋሪያው ዮሐንስ፡ - «ቃልም እግዚአብሔር ነበረ፤ ይህም በመጀመሪያው በእግዚአብሔር ዘንድ ነበር። ዮሐ.1፥1-2
ሃዋሪያው ጴጥሮስ ፡ - « ኢየሱስን የሕይወታችሁ ጌታ አድርጋችሁ ታመልኩት ዘንድ ይገባል።» ብሏል። 1ጴጥ 3፡15

ሆኖም ኢየሱስ ስለራሱ ያለው ነገር ምንድነው?

እርሱ ራሱን እንደ አምላክ አድርጎ ገልጾ ነበርን? በደንብ። ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር በተመላለሰበት ጊዜ በጊዜው ሰዎች በሚገባቸው ዐውድ ስለራሱ የተናገራቸውን ከዚህ በታች ተዘርዝረው ተቀምጠዋል።

ኢየሱስ አምላክ ነውን? ኢየሱስ ፡- እርሱ ከአምላክ ጋር እኩል እንደሆነ ተናግሯል።

«አባታችሁ አብርሃም ቀኔን ያይ ዘንድ ሐሴት አደረገ። ደስም አለው።” አይሁድም፡-“ገና ሃምሳ ዓመት ያልሆነህ አብርሃምን አይተሃልን? አሉት” ። ኢየሱስም “እውነት እውነት እላችኋለሁ አብርሃም ሳይወለድ እኔ አለሁ፣ አላቸው። ስለዚህ ሊወግሩት ድንጋይ አነሱ፤ ኢየሱስ ግን ተሰወረባቸው፣ ከመቅደስም ወጥቶ በመካከላቸው አልፎ ሄደ።» ዮሐ.8፥36

«. . . እኔና አብ አንድ ነን። አይሁድ ሊወግሩት ደግመው ድንጋይ አነሱ፤ ኢየሱስ፡- ከአባቴ ብዙ መልካም ሥራ አሳየኋችሁ ስለማናቸው ሥራ ትወግሩኛላችሁ? ብሎ መለሰላቸው። አይሁድም ስለ መልካም ሥራ አንወግርህም ፤ ስለ ስድብ አንተም ሰው ስትሆን ራስህን አምላክ ስለማድረግህ ነው እንጂ። ብለው መለሱለት። » ዮሐ. 10፥30-33

« ኢየሱስም ጮኸ እንዲህም አለ፡- በእኔ የሚያምን በላከኝ ማመኑ ነው እንጂ በእኔ አይደለም፤ እኔንም የሚያይ የላከኝንም ያያል። በእኔ ሚያምን ሁሉ በጨለማ እንዳይኖር እኔ ብርሃን ሆኜ ወደ ዓለም መጥቻለሁ። »ዮሐ. 12፥44-46

« እግራቸውንም አጥቦ ልብሱንም አንስቶ ዳግመኛ ተቀመጠ ፥ እንዲህም አላቸው ያደረግሁላችሁን ታስተውላላችሁን? እናንተ መምህርና ጌታ ትሉኛላችሁ እንዲሁ ነኝና መልካም ትላላችሁ። እንግዲህ እኔ ጌታና መምህር ስሆን እግራችሁን ካጠብሁ ፣ እናንተ ደግሞ እርስ በራሳችሁ እግራችሁን ትተጣጠቡ ዘንድ ይገባችኋል። »ዮሐ. 13፥11-14

« እኔ መንገድ እውነት ሕይወትም ነኝ ፣ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም። እኔንስ ብታውቁኝ አባቴን ደግሞ ባወቃችሁ ነበር። ከአሁን ጀምራችሁ ታውቁታላችሁ ፣ እይታችሁትማል አለው። ፊልጶስ፡- ጌታ ሆይ አብን አሳየንና ይበቃናል አለው፡- አንተ ፊልጶስ ይህን ያህል ዘመን ከእናንተ ጋር ስኖር አታውቀኝምን? እኔን ያየ አብን አይቷል። እንዴትስ አንተ - አብን አሳየን ትላለህ? »ዮሐ. 14፥6-9

ኢየሱስ አምላክ ነውን? ከኢየሱስ አባባል የተወሰደ፡ እርሱ ራሱን እንዴት ገለጸ. . .

« ኢየሱስም ፡- እውነት እውነት እላችኋለሁ ፥ እውነተኛ እንጀራ ከሰማይ የሚሰጣችሁ አባቴ ነው እንጂ ከሰማይ እንጀራ የሰጣችሁ ሙሴ አይደለም። የእግዚአብሔር እንጀራ ከሰማይ የሚወርድ ለዓለምም ሕይወትን የሚሰጥ ነውና አላቸው ። ስለዚህ ጌታ ሆይ ፥ ይህን እንጀራ ዘወትር ስጠን አሉት። ኢየሲስም ፡- እንዲህ አላቸው ፡- የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ ወደእኔ የሚመጣ ከቶ አይራብም፤ በእኔ ሚያምንም ሁልጊዜ አይጠማም። »ዮሐ. 6፥32-35

« ደግሞም ኢየሱስ ፡- እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ ፤ የሚከተለኝ የሕይወት ብርሃን ይሆንለታል እንጂ በጨለማ አይመላለስም ብሎ ተናገራቸው ። ፈሪሳውያንም ፡- አንተ ስለራስህ ትመሰክራለህ ፤ ምሥክርነትህ ዕውነት አይደለም አሉት። ኢየሱስ መለሰ አላቸውም፤ - እኔ ስለራሴ ምንም እንኳ ብመሰክር ከወዴት እንደመጣሁ ወዴትም እንድሄድ አውቃለሁና፡ ምሥክርነቴ ዕውነት ነው ፤ እናንተ ግን ከወዴት እንደመጣሁ ወዴትም እንድሄድ አታውቁም። »ዮሐ. 8፥12-14

« ኢየሱስም ደግሞ አላቸው ፡- እውነት እውነት እላችኋለሁ ፥ እኔ የበጎች በር ነኝ ። ከእኔ በፊት የመጡ ሁሉ ሌቦችና ወንበዴዎች ናቸው ፤ ዳሩ ግን በጎቹ አልሰሙአቸውም ። በሩ እኔ ነኝ፡ በእኔ የሚገባ ቢኖር ይድናል። ይገባልም ይወጣልም መሰማሪያም ያገኛል። ሌባው ሊሰርቅና ሊያርድ ሊያጠፋም እንጂ ስለሌላ አይመጣም። እኔ ሕይወት እንዲሆንላችሁ እንዲበዛላችሁም መጣሁ ። መልካም እረኛ እኔ ነኝ መልካም እረኛ ነፍሱን ስለበጎቹ ያኖራል ። »ዮሐ. 10፥7-11

«ማርታም ኢየሱስ እንደመጣ በሰማች ጊዜ ልትቀበለው ወጣች ። ማርያም ግን በቤት ተቀምጣ ነበር። ማርታም ኢየሱስን ጌታ ሆይ አንተ በዚህ ኖረህ ብትሆን ወንድሜ ባልሞተም ነበር። አሁንም ከእግዚአብሔር የምትለምነውን ሁሉ እግዚአብሔር እንዲሰጥህ አውቃለሁ አለችው። ኢየሱስም ፡- ወንድምሽ ይነሳል አላት። ማርታም፡- በመጨረሻው ቀን በትንሣኤ እንዲነሳ አውቃለሁ። አለችው። ኢየሱስም ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ ። የሚያምንብኝ ቢሞት እንኳ ሕያው ይሆናል። ሕያው የሆነም የሚያምንብኝ ሁሉ ለዘላለም አይሞትም። ይህን ታምኚያለሽን ? አላት። እርስዋም አዎን ጌታ ሆይ አንተ ወደ ዓለም የሚመጣው ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆንክ እኔ አምናለሁ አለችው። »ዮሐ. 11፥20-27

ኢየሱስ አምላክ ነውን? ኢየሱስ ከተናገረው የተወሰደ፡ እዚህ ስለነበረው ተልዕኮ የተናገረው . . .

« ኢየሱስም ወደርሱ ጠርቶ እንዲህ አላቸው ፡- የአህዛብ አለቆች ተብሎ የምታስቡት እንዲገዟችሁ ታላላቆቻችሁም በላያቸው እንዲሰለጥኑ ታውቃላችሁ። በእናንተስ እንዲህ አይደለም፤ ነገር ግን ማንም ከእናንተ ታላቅ ሊሆን የሚወድ የእናንተ አገልጋይ ይሁን ፥ ከእናንተ ማንም ፊተኛ ሊሆን የሚወድ የሁሉ ባርያ ይሁን ፥ እንዲሁም የሰው ልጅ ሊያገለግልና ነፍሱን ለብዙዎች ቤዛ ሊሰጥ እንጂ እንዲያገለግሉት አልመጣም። »ማርቆ. 10፥42-45

« ከዚያም ወጠተው በገሊላ በኩል አለፉ ፤ ደቀመዛሙርቱንም ያስተምር ስለነበር ማንም ያውቅ ዘንድ አልወደደም ። ለእነርሱም፡- የሰውልጅ በሰው እጅ አልፎ ይሰጣል ይገድሉትማል ተገድሎም በሦስተኛው ቀን ይነሳል። ይላቸው ነበር። እነርሱም ነገሩን አላስተዋሉም ፤ እንዳይጠይቁትም ፈሩ። »ማርቆ. 9፥30-32

«በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዷልና ። ዓለም በልጁ እንዲድነ ነው እንጂ ፥ በዓለም እንዲፈርድ እግዚአብሐየር ወደ ዓለም አላከውምና ፤ በእርሱ የሚያምን አይፈረድነትም ፤ በማያምን ግን በአንዱ በእግዚአብሔር ልጅ ስላላመነ አሁን ተፈርዶበታል ። »ዮሐ. 3፥16-18

« አብ የሚሰጠኘ ሁሉ ወደእኔ ይመጣል ፤ ወደእኔም የሚመጣውን ከቶ ወደ ውጭ አላወጣውም ፤ ፈቃዴን ለማድረግ አይደለም እንጂ የላከኝን ፈቃድ ለማድረግ ከሰማይ ወርጃለሁና ። ከሰጠኝም ሁሉ አንድ ስንኳ እንዳላጠፋ በመጨረሻው ቀን እንዳስነሳው እንጂ የላከኝ የአብ ፈቃድ ይህ ነው። ልጅንም አይቶ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወትን እንዲያገኝ የአባቴ ፈቃድ ይህ ነው። እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ። »ዮሐ. 6፥37-40

 ከእግዚአብሔር ጋር ግንኙነትን እንዴት እንደምትጀምር
 ጥያቄ አለኝ

ሼር ያድርጉ
WhatsApp Share Facebook Share Twitter Share Share by Email More