×
ፈልግ
ስለህይወት እና ስለእግዚአብሄር በነፃነት
 ጥያቄ የሚጠይቁበት ድረገጽ
ወሲብ እና የፍቅር ግንኙነት

ፖርንን እጠላዋለሁ

ፖርኖግራፊ የዘመናችን ትልቅ ችግር ፖርን ልክ እንደ ናርኮቲክ ነው፣ የሰውን አዕምሮ ይሰርቃል፣ ሰብዓዊውን የፍትወተ ስጋ ስሜት ያናጋል (ያዛባል)፣ እግረ መንገዱንም ሕይወትን ያወድማል፣ ቤተሰብን ያፈራርሳል ደግሞም አገልግሎቶችን ያዘበራርቃል (ያሽመደምዳል)።

WhatsApp Share Facebook Share Twitter Share Share by Email More PDF

በኤሪክ ሲሞንስ የተፃፈ

ፖርኖግራፊ የዘመናችን ትልቅ ችግር

ፖርን ልክ እንደ ናርኮቲክ ነው፣ የሰውን አዕምሮ ይሰርቃል፣ ሰብዓዊውን የፍትወተ ስጋ ስሜት ያናጋል (ያዛባል)፣ እግረ መንገዱንም ሕይወትን ያወድማል፣ ቤተሰብን ያፈራርሳል ደግሞም አገልግሎቶችን ያዘበራርቃል (ያሽመደምዳል)። እውነቱን ልንገራችሁ፣ እኔን ትክት ያደረገኝ ችግር ነው። የታከትኩትም ሰይጣን ልጆችን፣ ሴቶችን፣ ቤተሰብን፣ መጋቢዎችን፣ ቤተክርስቲናትን እና ዓለምን በጠቅላላ አሰቃቂ በሆነው ክፉ ምግባር ያወደመ በመሆኑ ነው።

ፖርን ለእኔ ችግር መሆን የጀመረው ገና የስድስት ዓመት ጨቅላ እንደነበርኩ ነው። በእግዚአብሔር ጸጋ ግን ችግሩ በዐሥራ ሰባተኛው ዓመቴ ኢየሱስ ሲያድነኝ አበቃለት። ግን ጉዳዩ የማያዳግም ሆኖ የሚወገደው አልፎ አልፎ መሆኑን አውቃለሁ። ዛሬም ቢሆን ፈተናነቱ እያንዣበበ ነው፣ አዎን፤ ፈተናው እንደ እኔ በከተሞች በሚኖሩ፣ የእኔን መሳይ ልብ ባላቸው ላይ ያንዣብባል፣ ሆኖም ከዚያ እጅግ በሚበልጥ መጠን ጸጋው በክርስቶስ ኢየሱስ አማካይነት ከብቦናል።

ወዳጆቼ፣ ፖርንን እጠላዋለሁ። ምክንያቴም ይኸውላችሁ።

እግዚአብሔር በወንዶችና በሴቶች ውስጥ የፈጠረውን የተፈጥሮ ጸጋ የሚያዘበራርቅ ስለሆነ ፖርንን እጠላዋለሁ።

በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠሩትን ሴቶች የወንዶችን ሴሰኛነት ለማርካት እንደተፈጠሩ መገልገያዎች አድርጎ ስለሚስል ፖርንን እጠላዋለሁ።

በእግዚአብሔር ግሩምና ድንቅ ክቡር ሰውነት እንዲኖራቸው ተደርገው የተፈጠሩትን ሴቶች እንደ አላቂ እቃ የሚያስቆጥራቸው ስለሆነ ፖርንን እጠላዋለሁ።

ሴቶችን በተለይ ደግሞ ሚስቴንና ሦስቱን ሴቶች ልጆቼን ስለምወድዳቸው ፖርንን እጠላዋለሁ።

በቃል ኪዳን ከታሰረ የትዳር ጓደኛ ጋር ብቻ እየተፈፀመ ነፍስን የሚያረካውን ፆታዊ ተራክቦ ነፍስን ወደሚያሸማቅቅ ራስን በራስ የማርካት እንግልት ውስጥ የሚያዘቅጥ ስለሆነ ፖርንን እጠላዋለሁ።

የእግዚአብሔርን ወንዶችና ሴቶች ልጆች ወደ ፍትወተ ስጋ ባርነት ውስጥ የሚጥል ስለሆነ ፖርንን እጠላዋለሁ።

ነፍሳቸውን ለወንጌል ሥራ እስከሞት ይሰጡ የነበሩ ሚሲናውያንን አቅመ ቢስ ክርስቲያኖች ስለሚያደርጋቸው ፖርንን እጠላዋለሁ።

በርካቶቹ ገና ሳይጀምሩት፣ ጋብቻን የሚያፈራርስ ስለሆነ ፖርንን እጠላዋለሁ።

ጎልማሳ ወንዶችን ያለ እድሜያቸው የጎረምሳነት ስሜት እንዲኖራቸው ስለሚያደርግ ፖርንን እጠላዋለሁ።

ወንዶች እግዚአብሔርን ከምትፈራ ሴት ጋር ከሚገኝ እርካታ ይልቅ ከፖርን ከዋክብት እርካታን ወደመፈለግ አዘቅት ውስጥ በማታለል ስለሚወረውራቸውና የውበትን ትርጉም ስለሚያዛባባቸው ፖርንን እጠላዋለሁ።

ከወንዶችና ከሴቶች ላይ የመታዘዝን ምሉዕ ደስታ ስለሚነጥቃቸው ፖርንን እጠላዋለሁ።

በባልና በሚስት መካከል ያለውን መተማመን ስለሚፈረካክሰው ፖርንን እጠላዋለሁ።

በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን በማታለል ወደ ገሃነም የሚነዳ ሰይጣናዊ እንቅስቃሴ ስለሆነ ፖርንን እጠላዋለሁ።

የመጋቢዎችን ጸጋ የሚስላጭና ቤተክርስቲያንን የሚያሽመደምድ ስለሆነ ፖርንን እጠላዋለሁ። (መጋቢዎች ሆይ፣ በፖርን ከተለከፋችሁ፣ ጸጋችሁን አስላጭታችኋል፣ ቤተክርስቲናችሁንም እየገደላችሁ ነው!)

አዳዲስ ቤተክርስቲናትን በብዛት እንዳንተክል እና ብዙ ሚሲዮናውያንን እንዳንልክ ያደረገን ዋነኛ ምክንያት ፖርን ይሆናል ብዬ ስለምጠረጥር ፖርንን እጠላዋለሁ።

በከተማዬና በሌሎችም በርካታ ከተሞች የሚገኙ ባዶ የቤተክርስቲያን ህንፃዎችን በዳኑ ሰዎች የሚሞሉትን የወንጌል ሰባኪዎች ፀጋ ያስላጨብን ስለሆነ ፖርንን እጠላዋለሁ።

አባታቸው (በፖርን ምክንያት) የሥራ እድል ማጣቱን ወይም ቤተክርስቲያንን አትመራም ተብሎ መታገዱን ሲነግራቸው ልጆች የሚያልፉበት የስቃይ (የጠስፋ መቁረጥ) ሕይወት ምንጩ እርሱ እንደሆነ ስለማውቅ ፖርንን እጠላዋለሁ።

ልጆች ከወላጆቻቸው ትክክለኛውን የስርዓተ-ፆታ ትርጉም ሳይረዱ በፊት የተዛባውን የፍትወተ ስጋ አመለካከት ስለሚጠቀጥቅባቸው ፖርንን እጠላዋለሁ።

በሳሎኔ ውስጥ ተቀምጬ ምርር ብለው የሚያለቅሱ፣ ግራ የተጋቡ፣ ሁሉ ነገራቸው ውድም ያለባቸውን ሚስቶችና የተሰበሩ፣ በእፍረት የተከደኑ፣ እና የሚኮነኑ የእርሱ ሰለባ የሆኑ ወንዶችን መመልከት ስላታከተኝ ፖርንን እጠላዋለሁ።

ሰዎች በቀሪው የሕይወት ዘመናቸው ነገራቸው ሁሉ ውድምድም እንዲል ወደሚያደርግ አስገድዶ የመድፈር ወንጀል፣ በማባበል መድፈር እና ወደ ተጣመመ ግንኙነት የሚመራ ስለሆነ ፖርንን እጠላዋለሁ።

ወንዶች የእግዚአብሔርን ስም ለማስከበር ያላቸውን ጉጉት ወደሚያዳፍን ራስን በራስ የማርካት ስቃይ ውስጥ ስለሚከትታቸው ፖርንን እጠላዋለሁ።

በስላሴ ፀጋ ከመርካት ይልቅ ኃጢአት፣ ሰይጣንና ዓለም ይበልጥ ያረኩናል ብሎ ስለሚናገር ፖርንን እጠላዋለሁ።

እግዚአብሔርን ባለመፍራት የሚመጣን ኩነኔና እርግማን ስለምጠላ ፖርንን እጠላዋለሁ።

በመላው ዓለም የሚገኙ ወላጆች ልጄ በሚያየው ነገር ይሰናከልብኛል ደግሞም ሱሰኛ ይሆንብኛል በሚል ስጋት ልባቸው እንዲጨነቅ ስለሚያደርግ ፖርንን እጠላዋለሁ።

ነገር ግን ኢየሱስን እወደዋለሁ።

በፖርን ችግር የተጠመዱትንም ሰዎች ስለሚወድድ ኢየሱስን እወደዋለሁ።

የፖርን እስረኛ የሆኑ ልቦችን የማንፃት ኃይል (ሥልጣን) ስላለው ኢየሱስን እወደዋለሁ።

የፖርን ሱስ የሌለበትን እርሱን የፖርን ሱስ አደረገው ስለዚህም የፖርን ሱሰኛ የሆነ ሰው ከእርሱ የተነሳ የእግዚአብሔር ጽድቅ ሆነ።

እኛ በእርሱ ሆነን የእግዚአብሔር ጽድቅ እንሆን ዘንድ ኃጢአት የሌለበትን እርሱን ስለ እኛ ኃጢአት አደረገው።1

በዚያች እጅግ ድንቅ አረፍተ-ነገር፣ ጳውሎስ የፖርንን መዘዝ መደምደሚያ አበጀለት።

ወዳጄ ሆይ፣ አንተ ከእንግዲህ የኢሱስ እንጂ፣ የአዳም አይደለህም። ኢየሱስ ምትክህ ሆኗል። ትክክለኛውን ነገር በማበላሸታችን ምክንያት የሚጠብቀንን የእግዚአብሔር ፍትሃዊ ቅጣት በመቀበል እርሱ የፖርን ተጠቂ ሆነ፣ ከእርሱም የተነሳ አንተ ሙሉ መብት ያለው የእግዚአብሔር ወንድ ወይም ሴት ልጅ ሆንክ።

ወዳጄ ሆይ፣ በአንድ የፍቅርና የፍትህ ሥራ ምክንያት፣ በኢየሱስ የመስቀል ላይ ሥራ፣ በእርሱም በማመን፣ አንተ አሁን ንፁህ፣ ቅዱስ፣ እግዚአብሔር የተቀበለህ፣ ይቅር የተባልክና ነፃ ነህ። ደግሜ ልንገርህ … ነፃ ነህ!!!!!

ኢየሱስን እወደዋለሁ።

 ከእግዚአብሔር ጋር ግንኙነትን እንዴት እንደምትጀምር
 ጥያቄ አለኝ

የግርጌ ማስታወሻ: (1) 2ኛ ቆሮንቶስ 5፡21

ምንጭ ፡ http://www.desiringgod.org/articles/i-hate-porn


ሼር ያድርጉ
WhatsApp Share Facebook Share Twitter Share Share by Email More