×
ፈልግ
ስለህይወት እና ስለእግዚአብሄር በነፃነት
 ጥያቄ የሚጠይቁበት ድረገጽ
FAQ

በካቶሊክ ዕምነትና በክርስትና መካከል ልዩነት አለን?

WhatsApp Share Facebook Share Twitter Share Share by Email More PDF

ጥያቄ. ካቶሊክ በመሆንና ክርሰቲያን በመሆን መካከል ልዩነት አለን?

የኛ መልስ፡  በክርስትና ዕምነት ጥላ ሥር ብዙ ቤተ ዕምነቶችና አቢያተ ክርስቲያኖች አሉ፤- ካቶሊክ ፣ ፕሬስቤተርያን፣ ሜቶዲስት፣ ባፕቲስት፣ ሉተራውያን ፣ የመሳሰሉት ማለት ነው። ከነዚህ ባንዱ ውስጥ አባል መሆን ማለት ዕውነተኛ ክርስቲያንነትን አያመለክትም።

ዋናው ቁምነገሩ እሱ ወይም እሷ በግላቸው ኢየሱስ ክርስቶስን ወደ ሕይታቸው ውስጥ አስገብተዋል? ወይም ከእግዚአብሔር ጋር በግል ግንኙነት አላቸው ወይ ነው ።

በዮሐንስ ወንጌል ውስጥ እንዲህ ተጽፎ እናገኛለን፡- « ለተቀበሉት ሁሉ (ጌታ ኢየሱስ ከርስቶስን ማለት ነው ) በስሙ ለሚያምኑት ለነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው ። »1 ለምንድነው የእግዚአበሔር ልጆች መሆን ያለብን? ምክንያቱም እስከዛ ድረስ እግዚአብሔር ከእኛ ርቆ ስለነበረ ነው። እንዳለ ብቻ ነው የምናውቀው፤ መመለክ እንዳለበትም ልናውቅ እንችል ይሆናል። ችግር ውስጥ በገባን ጊዜና ዕርዳታን ስንሻ ደግሞ ወደ እርሱ መጸለይ እንደምንችልም እናውቅ ይሆናል። ሆኖም በኃጢዓታችን ምክንያት በእኛና በእግዚአብሔር መካከል ርቀትና ክፍተት እንደተፈጠረ እናውቃለን።

አሁን እስከኖርንና ትንፋሻችን እስካለ ድረስ ኃጢአት ልንሰራ እንችላለን። ሁሉንም ነገር እግዚአብሔር በሚፈልገው መንገድ ሳይሆን እኛ በምንፈልገው መንገድ ብቻ የመስራት ዝንባሌ ነው ያለን። ሆኖም ኃጢዓት በእኛና በእግዚአብሔር መካከል ግርዶሽ ሆኖ አይቀርም። እንዴት

መጽሐፍ ቀዱስ ኃጢዓት ቅጣት እንዳለው ይገልጽልናል። ቅጣቱ እኔና እናንተ ከምንገምተው በላይ ነው። የኃጢዓት ዋጋ ሞት ነው። ሞት ተብሎ የተወሰነው ቅጣት ነፍስ ላጠፋ ብቻ አይደለም። ለሁሉም ኃጢዓት እግዚአብሔር ፍርድን ያስተላለፈው የሞት ፍርድን ነው። መጽሐፍ ቀዱስም ይህንን ሲያረጋግጥ እንዲህ ይላል፤- « የኃጢዓት ደመወዝ ሞት ነውና፤ . . .»2 ስለዚህ በኃጢዓታችን ምክንያት ከእግዚአብሔር ተለይተን ለዘላለም እንዳንሞት ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በእኛ ፈንታ ሞተ። የኃጢዓታችንን ዋጋ ሙሉ በሙሉ ከፈለ። በዚህም የተነሳ ከኃጢዓታችን ሙሉ በሙሉ ይቅርታን አገኘን። ያገኘነው ጊዜያዊ ይቅርታ አይደለም። ምናልባትም ወደፊት በስህተት በ በኃጢዓት ብንወድቅ ጌታ ኢየሱስ አንዴ ለበደላችን ሁሉ ሞቶ ይቅርታን አግኝተናልና ምህረትን ከእግዚአብሔር ዘንድ እንቀበላለን። በእኛና በእግዚአብሔር መካከል የልዩነት ግድግዳ ተወገደልን። ይህ ማለት እኛ ፍፁማን ሆነናልና በኃጢዓት አንወድቅም ማለት አይደለም። ሆኖም በእኛ ቦታ ጌታ የሞተልንን ኢየሱስ ክርስቶስ እሱን ስናይ ይቅርታና ምህረትን አግኝተናል።

« ሁሉ ኃጢዓትን ሰርተዋልና የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሏቸዋል፤ በኢየሱስ ክርስቶስ በሆነው ቤዛነት በኩል እንዲያው በጸጋው ይጸድቃሉ። »3

ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ ግል መድኃኒታችን አድርገን ተቀብለን ወደ ሕይወታችን ስናስገባው፥ እግዚአብሔር አምላክ ከጥፋት ነጻ መሆናችንን ያውጀልንና ፥ በእርሱ ፊት ጻድቅ ያደርገናል። ከእግዚአብሔር ጋር ያለን ግንኙነትም በሚገባ ይጀመራል። የእርሱ ሕይወት በኛ ውስጥ እንዳለም እናውቃለን። ከእግዚአብሔር ጋር የቅርብ ግንኙነት እንዲኖረን የእርሱን ታላቅ ምህረት አግኝተናል።- «. . . የኃጢዓት ደመወዝ ሞት ነውና የእግዚአብሔር የጸጋ ሥጦታ ግን በክርስቶስ ኢየሱስ የዘላለም ሕይወት ነው። »4

ከእግዚአብሔር ጋር የግል ገንኙነት ለማድረግ በእርግጥ ከወሰናችሁ፥ ኃጢዓታችሁ ይቅር ተብሏል። በናንተና በእግዚአብሔር አምላክ መካከል ያለው የልዩነት ግድግዳ ተወግዷል። ስለዚህ ጉዳይ በበለጠ ለማወቅ ከፈለጋችሁ ፥ እግዚአብሔርን በግል ማወቅ የሚለውን ጽሑፍ እንድታነብቡ እንመክራችኋን።

 ከእግዚአብሔር ጋር ግንኙነትን እንዴት እንደምትጀምር
 ጥያቄ አለኝ

የግርጌ ማስታወሻ: (1) ዮሐ.1፥12 (2) ሮሜ 6፥23 (3) ሮሜ 3፥23-24 (4) ሮሜ. 6፥23


ሼር ያድርጉ
WhatsApp Share Facebook Share Twitter Share Share by Email More